About Us

Welcome to Fikir Yashenfal - Since 2010

እኛ ፍቅር ያሸንፋሎች ነን……… ለአመታት ጨለማ ቤት ውስጥ በግፍ አስረውን በማይተካው እድሜያችን የቀለዱብንን፣ቶርች የገረፉንን፣የሰቀሉንን፣ብዙ እጅግ ብዙ ተነግሮ የማያልቅ ግፍ የሰሩብንን ለፈጣሪ ብለን እንዲሁም ለሀገራችን ሠላም ቀጣይነት ይጠቅማል ብለን ይቅር (አፉ) ብለን………"ፍቅር ያሸንፋል" የሚል ማህበር መስርተን ለሀገራችን አንድነትና አብሮነት ያቅማችንን ለመወጣት እየታገልን እንገኛለን።

ፍቅር ያሸንፋል ማህበር በሀገራችን የተለያየ የሀሳብ ልዩነት ያላቸውን የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችን እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን በማናገር "ለሀገር አንድነትና ለፍቅር" እንሮጣለን የሚል መልካም ምላሾችን ያገኘን መሆናችንን ስንነግራችሁ በታላቅ ደስታ ነው። እኛ ፍቅርን እንጂ ጥላቻን አንሰብክም! ስለፍቅር ሲባል ስለፀብ ካወራን ተሳስተናል አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል…… እመኑኝ……ፍቅር ያሸንፋል!